ወጋገን ባንክ ለሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ 500,000 ሺ ብር የበጎ አድራጎት ድጋፍ አደረገ

ወጋገን ባንክ ለሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ 500,000 ሺ ብር የበጎ አድራጎት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ወጋገን ባንክ በዶ/ር ካትሪን ሐምላን ለተመሰረተውና በኢትዮያጵያ ለሚገኙ የፊስቱሊ ታማሚ እናቶችና ሌጃገረዶች ህክምና አገልግሎት ለሚሰጠው ሀምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ኃሊፊነቱን ከመወጣት አንፃር የብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ) የበጎ አድራጎት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ በአገራችን እጅግ አስከፊ በሆነው በዚህ በሽታ የሚያዙ ሰዎች በጊዜውና በአግባቡ ህክምና ከተደረገላቸው የሚድኑ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይህንን የጤና እክል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚቻለው ግን የሚመለከታቸው የፋይናንስ ተቋማት እንደ ወጋገን ባንክ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ነው፡፡ በድጋፍ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው የእርዳታ ቼኩን ለፊስቱላ ኢትዪጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ማሞ ያስረከቡት የወጋገን ባንክ የብራንች ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ክንዴ አበበ፣ ባንኩ የለገሰው ገንዘብ 11 የፊስቱላ ታማሚዎች የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚውል ተናግረዋል፡፡
ወጋገን ባንክ ምንጊዜም ለወገን ደራሽነቱን በማረጋገጥ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አሁንም የማህበራዊ ኃሊፊነቱን ለመወጣት ባለው የፀና አቋም ይህንን የበጎ አድራጎት ድጋፍ ማድረጉን አቶ ክንዴ አበበ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ወጋገን ባንክ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣እንዲሁም በአስመጪና ላኪ የሥራ ዘርፍ ለተሰማሩ በርካታ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የገንዘብ አቅርቦት ምንጭ በመሆን ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት እያከናወናቸው ያሉት ሥራዎች አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኙ አቶ ክንዴ አበበ ተናግረዋል፡፡

About the Author

Comments are closed.