የባለአክሲዮኖች 29ኛ መደበኛ እና 14ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

የባለአክሲዮኖች 29ኛ መደበኛ እና 14ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ለወጋገን ባንክ አ.ማ ባለ አክሲዮኖች በሙሉ፡-

የወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና ገንዘቡ ብር 3,471,000,000፣ የምዝገባ ቁጥሩ KK/AA/3/0001748/2004 እና ዋና መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባ የሆነው ባንክ፤ የባለአክሲዮኖች 29ኛ መደበኛ እና 14ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎች ቅዳሜ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ስለሚካሄዱ፤ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙልን የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

የ29መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-

  1. አጀንዳዎቹን ማጽደቅ፣
  2. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣
  3. የአክሲዮኖች ዝውውርን ማሳወቅ፣
  4. እ.ኤ.አ የ2021/2022 የስራ ዘመን አፈጻጸም የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
  5. እ.ኤ.አ የ2021/2022 የሥራ ዘመን የውጭ ኦዲተር ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
  6. እ∙ኤ.አ የ2021/22 የስራ ዘመን የባንካችን የተጣራ ትርፍ አደላደል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
  7. እ.ኤ.አ የ2021/22 የስራ ዘመን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
  8. እ.ኤ.አ የ2022/23 የስራ ዘመን የባንኩን ሂሳብ የሚመረምር የውጭ ኦዲተር ምርጫ ማካሄድና ክፍያውን መወሰን እና
  9. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ማካሄድና ክፍያቸውን መወሰን ናቸው፡፡

የ14አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-

  1. አጀንዳውን ማጽደቅ፣
  2. የባንኩን ካፒታል ስለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ መወሰን እና
  3. የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. በስብሰባው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና (proxy) ቅጽ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት ከሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት፣ 17ኛ ፎቅ ወስዳችሁ በመሙላት ከስብሰባው ሶስት ቀናት በፊት ተወካይ መሾም ትችላላችሁ፡፡
  2. ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ሕጋዊ ውክልና የተሰጣችሁ ተወካዮች በስብሰባው መካፈል ትችላላችሁ፡፡
  3. በስብሰባው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖችና ተወካዮች እንዲሁም በባንኩ ቀርባችሁ ውክልና (proxy) የምትሰጡ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
  4. የባንኩን የመመስረቻ ፅሁፍ ማሻሻያ ሰነድ ከባንኩ ቅርንጫፎች እና ድረገፅ (www.wegagen.com) ላይ በማውረድ ማግኘት ይቻላል።

[wpdm_package id=’8715′]

About the Author

Comments are closed.