Category Archives: featured

featured

ወጋገን ባንክ አ.ማ እጩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የወጋገን ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሄደው 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባላት መመረጣቸውና ኮሚቴው የሚመራበት የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና ምርጫ መመርያ መጽደቁ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም አስመራጭ ኮሜቴው ስራውን የጀመረ ስለሆነ፤ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለባንኩ ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ብቁ እጩዎች እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ እንዲጠቁሙ አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ተጠቋሚዎች በእጩነት ለመቅረብ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ፤
2. የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
3. የማንኛውም ባንክ ሰራተኛ ያልሆነ፤
4. እድሜው 30 አመትና ከዚያ በላይ የሆነ፤
5. በወጋገን ባንክ አ.ማ. የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ፤
6. በሌላ የገንዘብ ተቋም ውስጥ የዲሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ፤
7. የመምረጥና የመመረጥ መብቱ ያልተገደበ፤
8. በስነ-ምግባሩም ሆነ ድርጊቱ ህዝብን ከማታለልና ማጭበርበር ለመጠበቅ ሲባል የወጣን ህግ በመተላለፍ በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የተፈረደበት መሆኑን የሚያሳይ ሪኮርድ ወይም ማስረጃ የሌለበት፤
9. ስልጣን ላለው ተቆጣጣሪ አካል መስጠት ያለበትን መረጃ በመደበቅ፣ ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት፣ ማሟላት ያለበትን መስፈርት ባለማሟላቱ ምክንያት የእርምት እርምጃ የተወሰደበት መሆኑ የሚያሳይ ሪኮርድ የሌለበት፤
10. የፋይናንሺያል ጤናማነት (financial soundness) መስፈርት የሚያሟላ ማለትም ኪሳራ ላይ ያልሆነ፣ የተበደረውን የባንክ እዳ መክፈል የቻለ፣ ግብር ባለመክፈሉ ምክንያት ያልተፈረደበት፣ በቂ ስንቅ /ገንዘብ/ የሌለው ቼክ ያልጻፈ፤

11. የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ያለው፤

12. የሥራ ልምድን በተመለከተ ቢቻል በንግድ ስራና በንግድ ስራ አስተዳደር በተለይም በፋይናንስ ተቋም ወይም በባንክ ስራ ልምድ ያለው፤

ማሳሰቢያ
1. በጠቅላላው እጩ የቦርድ ተጠቋሚዎች ብዛት 22 ነው፡፡ ከሚጠቆሙት 22 እጩዎች መካከል 8ቱ ከባንኩ ጠቅላላ የተፈረሙ አክሲዮኖች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 2% (ሁለት በመቶ) በታች የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች ብቻ ሲሆን፤ መጠቆም የሚችሉትም ከባንኩ ጠቅላላ የተፈረሙ አክሲዮኖች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 2% (ሁለት በመቶ) በታች ባላቸው ባለአክሲዮኖች ብቻ ነው፡፡ የቀሪዎቹን 14 እጩዎች ጥቆማ በተመለከተ ሁሉም ባለአክሲዮኖች ሊጠቁሙና ሊጠቆሙ ይችላሉ፡፡
2. መስፈርቱን የሚያሟላና ፈቃደኛ የሆነ ባለአክሲዮን ራሱን መጠቆም ይችላል፤
3. የህግ ሰውነት ያለው ባለአክሲዮን በእጩነት ሊጠቆምና ዕጩ ሊጠቁም ይችላል፤
4. ማንኛውም ጥቆማ ሲቀርብ የጠቋሚው ሙሉ ስምና ፊርማ ሊኖረው ይገባል፤
5. በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴት ጾታም ያገለግላል፤
6. ከነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

ስለዚህ የባንኩ ባለአክስዮኖች በሙሉ ለዲሬክተሮች ቦርድ ዕጩዎችን ለመጠቆም የተዘጋጀውን ቅጽ ከባንካችን ዋና መስሪያ ቤት፣ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ቅርንጫፍ መ/ቤት፣ ንኡስ ቅርንጫፍ ወይም ከባንኩ ድህረ ገጽ www.wegagenbanksc.com በመውሰድ ለዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ በሚከተሉት መንገዶች ጥቆማ እንድታቀርቡ መጋበዛችሁን እናሳውቃለን፡፡

1ኛ/ በአዲስ አበባ፣ ወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና መ/ቤት ሕንጻ፣ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ ቢሮ በግንባር በመቅረብ፤
2ኛ/ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንካችን ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ወይም ቅርንጫፍ መ/ቤት በግንባር በመቅረብ፤
3ኛ/ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1018 በአደራ ደብዳቤ፤ ወይም
4ኛ/ በኢ-ሜል አድራሻ፡ bonominee@wegagenbanksc.com

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡ 0911201195 ወይም 0911152492 መደወል ይቻላል፡፡

DOWNLOAD WORD FILE

የዕጩ ቦርድ አባላት መጠቆሚያ ቅጽ

DOWNLOAD PDF FILE

የዕጩ-ቦርድ-አባላት-መጠቆሚያ-ቅጽ

ወጋገን ባንክ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ወጋገን ባንክ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም  በሠላም ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ በተካሄደው የድጋፍ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው የእርዳታውን ቼክ ለብሔራዊ የድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ  ያስረከቡት የወጋገን ባንክ  የኮርፖሬት ሰርቪስስ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ክንዴ አበበ “ሁልጊዜም በሀገሪቱ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን በመደገፍና የተፈጥሮም ሆኑ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲከሰቱ  ለወገን ደራሽነቱን በማረጋገጥ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ የቆየው ወጋገን ባንክ በሀገራችን ላይ የህልውና አደጋ የደቀነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት በማገዝ በዚህ አስቸጋሪ የፈተና ወቅት ከህዝባችን ጎን መቆም እንዳለብን በመገንዘብ የብር 5 ሚሊዮን ድጋፍ አድርገናል” ብለዋል፡፡

 

አቶ ክንዴ አበበ  ጨምረውም  “ወጋገን ባንክ  የኮሮና ቫይረስን የመከላከሉ ተግባር  ውጤታማ እስኪሆን ድረስ ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ጎን ሆኖ ድጋፉን የሚቀጥል መሆኑን እየገለፅኩ፤ ሁላችንም ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ አንድ ሆነን በትብብር ከሰራን በሽታውን የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንደምንቆጣጠረው  ባለሙሉ ተስፋ ነኝ” ብለዋል፡፡

 

ወጋገን ባንክ እንደ አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ተቋም የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል በዋናው መስሪያ ቤትም ሆነ በየቅርንጫፎቹ ለሰራተኞቹና ለደንበኞቹ ስለበሽታው መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በማከናወን  የእጅ መታጠቢያ ቁሳቁሶችን እና የፅዳት እቃዎችን እያቀረበ መሆኑን የገለፁት አቶ ክንዴ አበበ በሥራ ቦታ ያለውን  አካላዊ ጥግግት ለመቀነስም ለሰራተኞቹ ፈቃድ በመስጠት፣ በተለይም ለነፍሰጡር ሰራተኞች ከአመት ፈቃዳቸው የማይታሰብ ረፍት በመስጠት የሰራተኞቹን ደህንነት ለመጠበቅ ባንኩ  ተግቶ እየሰራ መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

በተጨማሪም በሽታውን ለመከላከል ቁልፍ የሆነውን አካላዊ መራራቅ ለመተግበር፣ ደንበኞች ወደ ቅርንጫፍ መምጣት ሳያስፈልጋቸው በሥራ ቦታቸው ወይም በቤታቸው ሆነው የኤሌክትሮኒክ ባንክ አገልግሎቶችን በመጠቀም ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉ  ሲሆን በአጋር ካርዳቸው በኤቲኤም ማሽን ብቻ በመጠቀም ወደሚፈልጉት  ሰው ሒሳብ ገንዘብ መላክ እና በቀን እስከ 10,000 ብር ማውጣት ፣በስልክዎ ባንክዎ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በቀን እስከ 50,000  ብር ማስተላለፍ  እና  የግለሰብ ኢንተርኔት ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በቀን እስከ 100,000  ብር ፣ድርጅቶች ደግሞ የሚፈልጉትን ያህል ገንዘብ በኮርፖሬት ኢንተርኔት ባንክ አገልግሎት ማስተላለፍ የሚችሉ መሆኑን ባንኩ  አስታውቋል፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ፡- ማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት፣ራስ መኮንን ጎዳና  አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት 14ኛ ፎቅ

ስልክ.+251 11 878 7921/19

Partial view of the lottery drawing ceremony

Partial view of the lottery drawing ceremony

የወጋገን ባንክ የውጭ ምንዛሪ ግኝት  ማበረታቻ ሽልማት ዕጣ ወጣ

 

ወጋገን ባንክ ከነሐሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ሲያካሂደው የነበረው ከወጋገን ይቀበሉ፣ በወጋገን ይመንዝሩ፣ በወጋገን ይሸለሙ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማበረታቻ ሽልማት ዕጣ  በትናንትናው ዕለት የካቲት 25 ቀን 2012 ዓም የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የብሔራዊ ሎተሪ  አስተዳደር ድርጅት  ኃላፊዎች በተገኙበት በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ ወጣ፡፡

 

በዚህም መሰረት የ2019 ሞዴል ኪያ ስፖርቴጅ መኪና የሚያስገኘው የአንደኛ ዕጣ ቁጥር 1010526 ሆኖ ወጥቷል፡፡

 

በ2ኛ እጣ አምስት የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች እና በ3ኛ ዕጣ ሀምሳ ስማርት የሞባይል ስልኮችን የሚያስገኙት ዕጣ ቁጥሮችም መውጣታችውን የገለፀው ወጋገን ባንክ ለአሸናፊዎቹ ሽልማቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ድርጅት ተወካዮች በሚገኙበት ሥነ ሥርአት ላይ በቅርቡ በይፋ እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡

 

እንኳን ደስ አላችሁ

 ከወጋገን ይቀበሉ፣ በወጋገን ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ አሸናፊ  የሎተሪ  ቁጥሮች

ወጋገን ባንክ ከነሃሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. እስከ የካቲት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ሲያካሂድ የቆየው ከወጋገን ይቀበሉ፣ በወጋገን ይመንዝሩ፣ በወጋገን ይሸለሙ የሎተሪ ሽልማት መርሐ-ግብር ዕጣ ረቡዕ የካቲት 25 ቀን 2012 . በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ድርጅት አዳራሽ በይፋ ወጥቷል፡፡

የተለያዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙት አሸናፊ የሎተሪ ቁጥሮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሲሆኑ ዕድለኛ ደንበኞች አስቀድመው አገልግሎቱን ወደ ተጠቀሙበት ወይም በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች ቀርበው እንዲያመለክቱ  በአክብሮት እየጠየቅን  በቅርቡ  በምናደርገው የሽልማት መርሀግብር  ለዕድለኞች ሽልማቱን በይፋ እንደምናስረክብ ስንገልፅ  ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል፡፡  

ተ.ቁ. የዕጣው ደረጃ የሽልማቱ ዓይነት የአሸናፊ ዕጣ የሎተሪ ዕጣው የደረሰበት ከተማ
1 1 ኪያ ስፖርቴጅ  አውቶሞቢል ሞዴል 2019 1010526 ጅግጅጋ
2 2 የልብስ ማጠቢያ 1012136 አድዋ
3 1011334 ባህር ዳር
4 1007817 አዲስ አበባ
5 1002355 ድሬ ዳዋ
6 1015262 ጅማ
7 3 ሳምሰንግ ጋላክሲ

የሞባይል ቀፎ

1012537 አዲስ አበባ
8 1023510 አዲስ አበባ
9 1009031 አዲስ አበባ
10 1025281 አዲስ አበባ
11 1002594 አዲስ አበባ
12 1014826 አዲስ አበባ
13 1014202 አዲስ አበባ
14 1023457 አዲስ አበባ
15 1025519 አዲስ አበባ
16 1026320 አዲስ አበባ
17 1034126 አዲስ አበባ
18 1006054 አዲስ አበባ
19 1010380 ቦንጋ
20 1037720 ቡታ ጅራ
21 1008630 ደሴ
22 1037145 ደሴ
23 1004456 ድብድቦ
24 1010481 ድሬ ዳዋ
25 1016042 ድሬ ዳዋ
26 1017569 ድሬ ዳዋ
27 1022950 ድሬ ዳዋ
28 1026470 ድሬ ዳዋ
29 1029740 ድሬ ዳዋ
30 1004971 ጎንደር
31 1008712 ጋምቤላ
32 1029158 ጋምቤላ
33 1032920 አዲስ አበባ
34 1034001 ሐረር
35 1030626 ሐረር
36 1028685 አዲስ አበባ
37 1001340 ሁመራ
38 1020929 አዲስ አበባ
39 1008240 ጅግጅጋ
40 1019176 ጅግጅጋ
41 1025198 ጅግጅጋ
42 1004310 አዲስ አበባ
43 1007290 አዲስ አበባ
44 1013251 አዲስ አበባ
45 1035720 አዲስ አበባ
46 1013779 ጋምቤላ
47 1014904 አዲስ አበባ
48 1012669 አዲስ አበባ
49 1031210 ሻሸመኔ
50 1014839 ሱሉልታ
51 1015129 አዲስ አበባ
52 1039221 ቶግ ዋጃሌ
53 1016684 አዲስ አበባ
54 1026703 ሰበታ
55 1002795 አዲስ አበባ
56 1014595 አዲስ አበባ

 

አድራሻ፡ ወጋገን ታወር፣ራስ መኮንን ጎዳና

አዲስ አበባ ስታዲዮም ፊት ለፊት

ስልክ : +251 115523800

+251 115177500

ስዊፍት፡-WEGAETAA

 

Wegagen Bank Partners With WorldRemit to Offer Digital Money Transfer Service

Wegagen Bank Partners With WorldRemit to Offer Digital Money Transfer Service

Featured

Addis Ababa and London, 15 May 2019- Wegagen Bank and WorldRemit one of the leaders in global money transfer announced their partnership to provide digital money transfer service to Ethiopian customers in a joint press conference on May 15, 2019 at the Hilton Hotel in Addis Ababa.
Wegagen Bank President Abay Mehari said on the occasion: “We are delighted to partner with WorldRemit one of the leading digital money transfer service provider to give our customers more options to receive money sent to them from abroad fast and safe.” He added Wegagen customers would benefit from the fastest and safest money transfer service Wegagen would provide in cooperation with WorldRemit. The partnership between Wegagen Bank and WorldRemit enables the three million-strong Ethiopian Diaspora living abroad in over 50 countries to send money home to over 1.2 million Wegagen Bank account holders safely and fast. Beneficiaries can also collect money sent from abroad at any of Wegagen Bank’s 335 branches across Ethiopia.
Sharon Kinyanjui, Head of East and Central Africa at WorldRemit, on her part said: “We are pleased to partner with one of Ethiopia’s leading private commercial banks. Like WorldRemit, Wegagen Bank is committed to offering its customers choice and convenience through digital financial services.” Kinyanjui also said, “This new partnership will further expand WorldRemit’s reach in Ethiopia, and help Ethiopian Diaspora communities worldwide connect with family and friends back home.”
World Remit offers a variety of convenient ways for recipients in Ethiopia with or without a bank account to receive money, including bank account transfer, cash pickup and mobile money. WorldRemit is a global leader in international remittances to mobile money services, and launched its first mobile money service to Ethiopia in 2018. In addition to mobile money, the company is connected to 32 million bank accounts and 4,000 cash pick-up locations nationwide.
Top senders to Ethiopia include the United Kingdom, United States and Canada. The National Bank of Ethiopia estimates that the country received over $5 billion in remittances in 2017/2018 fiscal year. However, evidence suggests that a significant portion of remittances to the country still flow through informal channels, which are often costly and put customers at risk of fraud and transaction delays. WorldRemit provides a solution to these challenges through its award-winning mobile phone application
and website. Customers can send money 24/7 with just a few taps on their smart phones. Today, around 70% of WorldRemit transfers are sent from the mobile app.
Having started operations in June 1997, Wegagen Bank offers a wide range of efficient banking services including electronic banking accessible through mobile app, USSD & internet platforms. The Bank provides both local and international money transfer service and partners with over eleven international money transfer agents. Currently Wegagen Bank has a network of 338 Branches of which 134 are in Addis
Ababa and the remaining 204 are located in other cities and towns across the country.

 

About WorldRemit
WorldRemit is the leading digital money transfer service that makes sending money as easy as sending an instant message. We currently send from 50+ countries to more than 145 receiving destinations, leading the shift to online and mobile money transfers and improving speed and convenience for users.On the sending side WorldRemit is 100% digital. For those receiving money, the company offers a wide range of options including bank deposit, cash collection, mobile airtime top-up and mobile money.

Backed by Accel Partners, TCV and Leapfrog – early investors in Facebook, Netflix and Slack –WorldRemit’s headquarters are in London, UK with a global presence including offices in the United States, the Philippines, Poland, Colombia, Kenya, and South Africa.
It’s easy to use – just open the app or visit the website and send money 24/7 – no more agents. Learn more at worldremit.com