የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለወጋገን ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና ገንዘቡ ብር 3,295,869,000፣ የምዝገባ ቁጥሩ KK/AA/3/0001748/2004 እና ዋና መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባ የሆነው ባንክ፤ የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ሠዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ስለሚያካሂድ፤ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙልን የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

የ28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-

 1. አጀንዳዎቹን ማጽደቅ፤
 2.  አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
 3. የአክሲዮኖች ዝውውርን ማሳወቅ፤
 4. እ.ኤ.አ የ2020/2021 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ሪፖርቱን ማጽደቅ፤
 5.  እ.ኤ.አ.የ2020/2021 የሥራ ዘመን የውጭ ኦዲተሩን ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 7. እ.ኤ.አ.የ2021/22 የስራ ዘመን የባንኩን ሂሳብ የሚመረምር የውጭ ኦዲተር ምርጫ ማካሄድና ክፍያውን መወሰን፤
 8.  በበጀት አመቱ ውስጥ የተደረገ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል መተካት ማሳወቅ፤እና
 9.  በተጣራ ትርፍ አደላደል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ

 • በስብሰባው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና (proxy) ቅጽ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊትለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት፣ 17ኛ ፎቅ ወስዳችሁ በመሙላት ከስብሰባው ሶስት ቀናት በፊት ተወካይ መሾም ትችላላችሁ፡፡
 • ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ሕጋዊ ውክልና የተሰጣችሁ ተወካዮች በስብሰባው መካፈል ትችላላችሁ፡፡
 • በስብሰባው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖችና ተወካዮች እንዲሁም በባንኩ ቀርባችሁ ውክልና (proxy) የምትሰጡ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
 • በጉባዔዉ ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጣዉ መመሪያ መሰረት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ወይም ማስክ ማድረግ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡
  የወጋገን ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

About the Author

Comments are closed.