ወጋገን ባንክ ከትግራይ ብስክሌት  ፌዴሬሽን ጋር የብስክሌት ውድድር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ

ወጋገን ባንክ ከትግራይ ብስክሌት  ፌዴሬሽን ጋር የብስክሌት ውድድር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ

ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ፣ መቐለ

በወጋገን ባንክ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የባንኩ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኪዳኔ ገ/ስላሴ ሲሆኑ በትግራይ ብስክሌት ፌዴሬሽን በኩል ደግሞ  ፕሬዝዳንቱ አቶ አሰፋ ገ/ስላሴ ናቸው፡፡ በወጋገን ባንክ ስፖንሰርነት የሚካሄደው የብስክሌት ውድድር ወጋገን ሻምፒዮና በሚል ስያሜ ከጥር 5 እስከ ሰኔ 30 2016 ዓ.ም በሰባት ከተሞች ማለትም መቐለ፣ ዓዲግራት፣ዓድዋ ፣አክሱም፣ሽረ እንዳስላሰ፣ዓብይ ዓዲ እና ውቅሮ ይከናወናል፡፡ ውድድሩ በሁለት ዘርፎች የሚካሄድ ሲሆን ሶስት የሴቶች  እና አምስት የወንዶች ክለቦች የኮርስ ብስክሌት ውድድር ላይ ይሳተፋሉ፡፡እንዲሁም ሶስት የወንዶች እና ሁለት የሴቶች ክለቦች የተራራ ላይ የብስክሌት ውድድር ያካሂዳሉ፡፡

በአጠቃላይ ከተለያዩ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ክለቦች የተውጣጡ 30 ሴት እና 70 ወንድ የብስክሌት ስፖርተኞች በውድድሩ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ይህ ውድድር ተቀዛቅዞ የነበረውን የክልሉን የብስክሌት ስፖርት ለማነቃቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ የትግራይ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከ20 ዓመት በላይ ያስቆጠረ አንጋፋ ፌዴሬሽን ሲሆን ኢትዮጵያን ወክለው በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች የተሳተፉ በርካታ የብስክሌት ተወዳዳሪዎችን አፍርቷል፡፡

About the Author

Comments are closed.