ወጋገን ባንክ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር እና ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ500 ሺ ብር ድጋፍ አደረገ

ወጋገን ባንክ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር እና ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ500 ሺ ብር ድጋፍ አደረገ

አዱስ አበባ፣ ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም- ወጋገን ባንክ የተመሰረተበትን 25ኛ አመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ ክብረ በዓለ ወቅት ባንኩ ሁልጊዜም እንደሚያደርገው ማህበራዊ ኃሊፊነቱን ለመወጣት ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር እና ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለእያንዳንዳቸው ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ) ድጋፍ አድርጓል፡፡ ወጋገን ባንክ ከመጋቢት 2010 እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ብቻ የትምህርትና ጤናን የመሳሰለ የማህበራዊ አገልግሎቶችን፣ በመላው ሀገሪቱ የሚካሄደ የልማት ስራዎችን ለመደገፍ እንዱሁም በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተጎደ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በተደረገው ርብርብ ከ70 ሚሉዮን ብር በሊይ ወጪ በማድረግ ተቋማዊ ኃሊፊነቱን በብቃት መወጣቱን የባንኩ የዲይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሹ ሁሴን ተናግረዋል፡፡

About the Author

Comments are closed.