ወጋገን ባንክ የ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓለን የማጠቃለያ ስነስርዓት በደመቀ ሁኔታ አካሄደ

ወጋገን ባንክ የ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓለን የማጠቃለያ ስነስርዓት በደመቀ ሁኔታ አካሄደ

አዱስ አበባ፣ ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም- ወጋገን ባንክ የተመሰረተበትን 25ኛ አመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ ስነስርአት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ፤ የባንኩ ደንበኞች ፤ ባለአክሲዮኖች፤ የዲይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት እንዱሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ቅዲሜ ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በሒልተን አዱስ አበባ በደማቅ ስነስርዓት አካሄል፡፡ በዕለቱ በስነስርአቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ የዲይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱሹ ሁሴን ወጋገን ባንክ ባለፉት 25 አመታት በመላው አገሪቱ 400 ቅርንጫፎችን ከፍቶ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ በርካታ ዜጎችን የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ከማድረጉም በላይ ኢንቨስትመንትን በማበረታታት እንዱሁም የወጪ ንግድን በመደገፍ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት
ጉልህ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል፡፡ ከ25 ዓመት በፊት ሰኔ 4 ቀን 1989 ዓ.ም በ16 ባለራዕይ ባለሀብቶች በብር 60 ሚሉዮን የተፈረመ መነሻ ካፒታል እና በብር 30 ሚሉዮን የተከፈለ ካፒታል በአዱስ አበባ በከፈታቸው ጎፋ እና መስቀል ሁለት ቅርንጫፎች የባንክ ኢንደስትሪውን የተቀላቀለው ወጋገን ባንክ ልክ በዛሬው ዕለት ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም 25 ዓመቱን ደፍኗል፡፡ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ቁጥር በአሁኑ ጊዜ 5,600 የደረሰ ሲሆን ሰራተኞችን ጨምሮ ከአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ዜጎች አክሲዮን ገዝተው የባንኩ ባለቤት ለመሆን ችለዋል፡፡አሁን ላይ የተከፈለ ካፒታለ ብር 3.4 ቢሉዮን ሲሆን ጠቅላላ ካፒታለ ደግሞ ብር 5.6 ቢሉዮን እንዱሁም ጠቅላላ ሀብቱም ከብር 41 ቢሉዮን በላይ ደርሷል፡፡ ወጋገን ባንክ ፍትሃዊ የሥራ ቅጥር ሥርዓትን ተከትሎ በአሁኑ ጊዜ ከ5,000 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡

About the Author

Comments are closed.