ወጋገን ባንክ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ፅ/ቤት ግምቱ ከ500 ሺ ብር በላይ የሆነ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን አበረከተ፡፡

ወጋገን ባንክ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ፅ/ቤት ግምቱ ከ500 ሺ ብር በላይ የሆነ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን አበረከተ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
ወጋገን ባንክ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ፅ/ቤት ግምታቸው ከ500 ሺ ብር በላይ የሆኑ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን ድጋፍ አደረገ ፡፡ ባንኩ ያለበትን ማህበራዊ ሃላፊነት ለመወጣት ለክፍለ ከተማው ከ500 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ 50 የቢሮ መገልገያ ጠረጴዛዎች እና 25 ወንበሮች ድጋፍ በማበርከት እንደወትሮው ሁሉ ለህብረተሰቡ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡ ድጋፉን የተረከቡት የክፍለ ከተማው የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት ተፈራ የመሬት አገልግሎትን ማሻሻል ማለት የእያንዳንዱን ህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻል መሆኑን ተናግረው ፣ የተደረገው ድጋፍ ለሰራተኛው አመቺ ሁኔታ በመፍጠር ለተገልጋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡ የወጋገን ባንክ ቺፍ ሂዩማን ካፒታል ኦፊሰር አቶ ኪዳኔ ገ/ስላሴ ለክፍለ ከተማው የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ህይወት ተፈራ ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

About the Author

Comments are closed.