ወጋገን ባንክ ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የጡረታ ተሰናባች ሰራተኞች የሽኝት  መርሃ -ግብር   የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ወጋገን ባንክ ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የጡረታ ተሰናባች ሰራተኞች የሽኝት መርሃ -ግብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ወጋገን ባንክ ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ለተካሔደው የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የጡረታ ተሰናባች ሰራተኞች ሽኝትና የሰራተኞች ማበረታቻ መርሃ-ግብር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር የብር 140,000.00 (አንድ መቶ አርባ ሺ) የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

በተጨማሪም ባንኩ በጡረታ ለተሰናበቱ 16 የሆስፒታሉ ሰራተኞች ለእያንዳንዳቸው የብር 1,000 (አንድ ሺህ) ዋርካ የተሰኘ እድሜያቸው 50 እና ከዛ በላይ ለሆኑ የሃገር ባለውለታዎች የተዘጋጀውን ከፍ ያለ የወለድ ምጣኔ ያለው የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት ደብተሩን በዕለቱ በስጦታ አስረክቧል፡፡በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ስጦታውን ለጡረታ ተሰናባች ሰራተኞች ያስረከቡት የወጋገን ባንክ የማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አፈወርቅ ገብረፃድቅ ናቸው፡፡

አቶ አፈወርቅ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ወጋገን ባንክ በመላ ሀገሪቱ 400 ቅርንጫፎችን ከፍቶ መላውን ህዝብ በማገልገል ላይ የሚገኝና ከ5000 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን እንዲሁም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ ከ4000 በላይ ዜጎችን የአክሲዮን ባለቤት ያደረገ ባንክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች በማክበር ላይ የሚገኘው ወጋገን ባንክ በቅርቡ ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል በልብ ህመም ለሚሰቃዩ ህፃናት ህክምና የሚውል የብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን) የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

About the Author

Comments are closed.