ወጋገን ባንክ ካፒታሉን ወደ 20 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

ወጋገን ባንክ ካፒታሉን ወደ 20 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም፡- ወጋገን ባንክ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም በሂልተን አዲስ አበባ ባካሄደው 29ኛ መደበኛ እና 14ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ፤ የባንኩን ካፒታል በአምስት ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ብር ለማድረስ በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ጠቅላላ ጉባኤው በአብላጫ ድምጽ አፅድቆታል፡፡
ባንኩ ካፒታሉን ለማሳደግ ለነባር ባለአክሲዮኖች እና ለሁሉም ማህበረሰብ አክሲዮን የሚሸጥ ይሆናል፡፡ ወጋገን ባንክ እ.ኤ.አ ሰኔ 30, 2021/22 በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተከፈለ ካፒታሉ 3.4 ቢሊዮን ደርሷል፡፡

About the Author

Comments are closed.