የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ወጋገን ባንክ አ.ማ. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት የውጪ አገር ዜግነት ከያዙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን ብር 1,699,000.00 ዋጋ ያላቸውን 1,699 አክሲዮኖች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 25 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባ መስፈርቶች፡-

 1. በጨረታው ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በመሳተፍ መግዛት ይችላል፡፡
 2. የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1,000 (አንድ ሺህ) ነው፡፡
 3. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከጨረታው ቀን በፊት ራስ መኮንን ጐዳና ፣አዲስ አበባ ስታዲዮም ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 13ፎቅ ትሬዠሪ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በመገኘት ከየካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሠነዶችን ብር 50 (ሃምሳ ብር) ከፍሎ በመውሰድ መሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በዚሁ በባንኩ አክሲዮን ክፍል ማስገባት አለባቸው፡፡
 4. ጨረታው መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
 5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተጫረቱትን አክሲዮኖች የመነሻ ጥቅል ዋጋ ¼ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. አንድ ተጫራች ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
 7. ተጫራቾች ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ፣ፖስፖርት ወይም ተቀባይነት ያለው ሌላ ማስረጃ ኮፒ እንዲሁም ድርጅቶች ከሆኑ የመመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ተቀባይነት ያለው ሰነድ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 8. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት ውሰጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም፡፡
 9. በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ ለባንኩ ያስዙት የጨረታ ዋስትና ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፣
 10. በሌሎች ሕጐችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጐች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
 11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118 72 0192/011 554 1615 ደውለው ማናገር ይቻላል፡፡

ወጋገን ባንክ አ.ማ.

About the Author

Comments are closed.