የወጋገን ባንክ የማህበራዊ ኃላፊነት ተሳትፎ

የወጋገን ባንክ የማህበራዊ ኃላፊነት ተሳትፎ

ወጋገን ባንክ አ.ማ በብር 60 ሚሊዮን የተፈረመ መነሻ ካፒታል እና በብር 30 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል ሰኔ 4 ቀን 1989 ተቋቋመ፡፡ ባንኩ ከማህበረሰቡ ያሰባሰበውን ሀብት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለተሰማሩ ዜጎች መልሶ በማበደርና የሥራ ፈጠራን በማበረታታት ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ነው፡፡ ባንኩ በአጠቃላይ ለ5,000 ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል በመፍጠር መንግስት ድህነትን ለመቀነስ እያደረገ ያለውን ሀገራዊ ጥረት እየደገፈ ነው፡፡ ባንካችን ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች በደንበኝነት የሚገለገሉበት ባንክ ሲሆን የባለአክሲዮኖቹ ቁጥር ደግሞ 3,973 ደርሷል፡፡

ወጋገን በአሁኑ ሰዓት በመላው ሀገሪቱ 395 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን 150 ቅርንጫፎች በአዲስ አበባ ሲገኙ 245 ቅርንጫፎች ደግሞ በመላው ሀገሪቱ ተሰራጭተው ይገኛሉ፡፡እነዚህ ቅርንጫፎች ለደንበኞች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በ10 ዲስትሪክቶች ሥር ተደራጅተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ የወጋገን ባንክ ዲስትሪክት ፅህፈት ቤቶች

 • ሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ፅ/ቤት
 • ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ፅ/ቤት
 • ምሥራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ፅ/ቤት እና
 • ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ፅ/ቤት ናቸው

በክልሎች የሚገኙ ዲስትሪክት ፅህፈት ቤቶች

 • መቀሌ ዲስትሪክት ፅ/ቤት
 • ሽሬ ዲስትሪክት ፅ/ቤት
 • ባህር ዳር ዲስትሪክት ፅ/ቤት
 • ድሬደዋ ዲስትሪክት ፅ/ቤት
 • ሀዋሳ ዲስትሪክት ፅ/ቤት እና
 • ጅማ ዲስትሪክት ፅ/ቤት ናቸው

ባለፉት ሦስት አመታት ወጋገን ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ካደረጋቸው የገንዘብ ድጋፎች ዋና ዋናዎቹ

ባንካችን በመላው ሀገሪቱ የሚካሄዱ የልማት ሥራዎችን በማገዝና በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም የበኩሉን ድጋፍ በማድረግ ለወገን ደራሽነቱን ያረጋገጠ ባንክ ነው፡፡

 • ለኦሮሚያ ክልል ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም ብር 10,000,000 (አሥር ሚሊዮን)
 • ለአምቦ ከተማ ልማት ሥራ ማካሄጃ ብር 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን)
 • ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ከጌዲዮ ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ ማቋቋሚያ ብር 4,000,000 (አራት ሚሊዮን)
 • ለሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋሚያ ብር 4,000,000 (አራት ሚሊዮን)
 • ለአማራ ክልል ከጣና ሐይቅ የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን)
 • ለአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋሚያ ብር 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን)
 • ለትግራይ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋሚያ ብር 4,000,000 (አራት ሚሊዮን)
 • የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለተቋቋመው ብሔራዊ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ብር 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን)
 • ለገበታ ለሸገር ፕሮጀክት ማካሄጃ ብር 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን)
 • ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ማካሄጃ ብር 10,000,000 (አሥር ሚሊዮን)
 • ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን)
 • ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለት ዙር ለተማሪዎች ምገባ እና የትምህርት ቁሳቁስ ማሟያ ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን)
 • ለሞት በኩላሊት ይብቃ በጎ አድራጎት ማህበር የዲያሊሲስ ማሽን መግዣ ብር 339,554.00 (ሦስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺ አምስት መቶ ሃምሳ አራት)
 • በአጠቃላይ ብር 57,339,554 (ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺ አምስት መቶ ሃምሳ አራት) ድጋፍ አድርጓል፡፡

About the Author

Leave a Reply