>
የባለአክሲዮኖች 30ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

የባለአክሲዮኖች 30ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለወጋገን ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና ገንዘቡ ብር 4,022,048,000፣ የምዝገባ ቁጥሩ KK/AA/3/0001748/2004 እና ዋና መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባ የሆነው ባንክ፤ የባለአክሲዮኖች 30ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ሠዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ስለሚካሄድ፤ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙልን የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

የ30ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-

1 አጀንዳዎቹን ማጽደቅ፤
2 አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
3 የአክሲዮኖች ዝውውርን ማሳወቅ፤
4 እ.ኤ.አ የ2022/2023 የስራ ዘመን አፈጻጸም የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ
ማጽደቅ፤
5 እ.ኤ.አ የ2022/2023 የሥራ ዘመን የውጭ ኦዲተር ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
6 እ∙ኤ.አ የ2022/2023 የስራ ዘመን የባንካችን የተጣራ ትርፍ አደላደል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ
ተወያይቶ መወሰን፤
7 እ.ኤ.አ የ2022/23 የስራ ዘመን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ክፍያና እ.ኤ.አ 2023/24 የስራ ዘመን ወርሃዊ
አበል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
8 እ.ኤ.አ የ2023/24 የስራ ዘመን የባንኩን ሂሳብ የሚመረምር የውጭ ኦዲተር ምርጫ ማካሄድና ክፍያውን
መወሰን እና
9 የቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት መስማትና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ
ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ

  • በስብሰባው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና (proxy) ቅጽ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት ከሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት፣ 19ኛ ፎቅ ወስዳችሁ በመሙላት ከስብሰባው ሶስት ቀናት በፊት ተወካይ መሾም ትችላላችሁ፡፡
  • ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ሕጋዊ ውክልና የተሰጣችሁ ተወካዮች በስብሰባው መካፈል ትችላላችሁ፡፡
  • በስብሰባው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖችና ተወካዮች እንዲሁም በባንኩ ቀርባችሁ ውክልና (proxy) የምትሰጡ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

የወጋገን ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

About the Author

Comments are closed.