ወጋገን ባንክ አ.ማ እጩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የወጋገን ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሄደው 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባላት መመረጣቸውና ኮሚቴው የሚመራበት የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና ምርጫ መመርያ መጽደቁ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም አስመራጭ ኮሜቴው ስራውን የጀመረ ስለሆነ፤ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለባንኩ ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ብቁ እጩዎች እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ እንዲጠቁሙ አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ተጠቋሚዎች በእጩነት ለመቅረብ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ፤
2. የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
3. የማንኛውም ባንክ ሰራተኛ ያልሆነ፤
4. እድሜው 30 አመትና ከዚያ በላይ የሆነ፤
5. በወጋገን ባንክ አ.ማ. የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ፤
6. በሌላ የገንዘብ ተቋም ውስጥ የዲሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ፤
7. የመምረጥና የመመረጥ መብቱ ያልተገደበ፤
8. በስነ-ምግባሩም ሆነ ድርጊቱ ህዝብን ከማታለልና ማጭበርበር ለመጠበቅ ሲባል የወጣን ህግ በመተላለፍ በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የተፈረደበት መሆኑን የሚያሳይ ሪኮርድ ወይም ማስረጃ የሌለበት፤
9. ስልጣን ላለው ተቆጣጣሪ አካል መስጠት ያለበትን መረጃ በመደበቅ፣ ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት፣ ማሟላት ያለበትን መስፈርት ባለማሟላቱ ምክንያት የእርምት እርምጃ የተወሰደበት መሆኑ የሚያሳይ ሪኮርድ የሌለበት፤
10. የፋይናንሺያል ጤናማነት (financial soundness) መስፈርት የሚያሟላ ማለትም ኪሳራ ላይ ያልሆነ፣ የተበደረውን የባንክ እዳ መክፈል የቻለ፣ ግብር ባለመክፈሉ ምክንያት ያልተፈረደበት፣ በቂ ስንቅ /ገንዘብ/ የሌለው ቼክ ያልጻፈ፤

11. የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ያለው፤

12. የሥራ ልምድን በተመለከተ ቢቻል በንግድ ስራና በንግድ ስራ አስተዳደር በተለይም በፋይናንስ ተቋም ወይም በባንክ ስራ ልምድ ያለው፤

ማሳሰቢያ
1. በጠቅላላው እጩ የቦርድ ተጠቋሚዎች ብዛት 22 ነው፡፡ ከሚጠቆሙት 22 እጩዎች መካከል 8ቱ ከባንኩ ጠቅላላ የተፈረሙ አክሲዮኖች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 2% (ሁለት በመቶ) በታች የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች ብቻ ሲሆን፤ መጠቆም የሚችሉትም ከባንኩ ጠቅላላ የተፈረሙ አክሲዮኖች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 2% (ሁለት በመቶ) በታች ባላቸው ባለአክሲዮኖች ብቻ ነው፡፡ የቀሪዎቹን 14 እጩዎች ጥቆማ በተመለከተ ሁሉም ባለአክሲዮኖች ሊጠቁሙና ሊጠቆሙ ይችላሉ፡፡
2. መስፈርቱን የሚያሟላና ፈቃደኛ የሆነ ባለአክሲዮን ራሱን መጠቆም ይችላል፤
3. የህግ ሰውነት ያለው ባለአክሲዮን በእጩነት ሊጠቆምና ዕጩ ሊጠቁም ይችላል፤
4. ማንኛውም ጥቆማ ሲቀርብ የጠቋሚው ሙሉ ስምና ፊርማ ሊኖረው ይገባል፤
5. በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴት ጾታም ያገለግላል፤
6. ከነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

ስለዚህ የባንኩ ባለአክስዮኖች በሙሉ ለዲሬክተሮች ቦርድ ዕጩዎችን ለመጠቆም የተዘጋጀውን ቅጽ ከባንካችን ዋና መስሪያ ቤት፣ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ቅርንጫፍ መ/ቤት፣ ንኡስ ቅርንጫፍ ወይም ከባንኩ ድህረ ገጽ www.wegagenbanksc.com በመውሰድ ለዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ በሚከተሉት መንገዶች ጥቆማ እንድታቀርቡ መጋበዛችሁን እናሳውቃለን፡፡

1ኛ/ በአዲስ አበባ፣ ወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና መ/ቤት ሕንጻ፣ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ ቢሮ በግንባር በመቅረብ፤
2ኛ/ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንካችን ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ወይም ቅርንጫፍ መ/ቤት በግንባር በመቅረብ፤
3ኛ/ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1018 በአደራ ደብዳቤ፤ ወይም
4ኛ/ በኢ-ሜል አድራሻ፡ bonominee@wegagenbanksc.com

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡ 0911201195 ወይም 0911152492 መደወል ይቻላል፡፡

DOWNLOAD WORD FILE

የዕጩ ቦርድ አባላት መጠቆሚያ ቅጽ

DOWNLOAD PDF FILE

የዕጩ-ቦርድ-አባላት-መጠቆሚያ-ቅጽ

About the Author

Leave a Reply