>
እጩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

እጩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የወጋገን ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄዱት የባለአክሲዮኖች 29ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭኮሚቴ አባላት መመረጣቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ኮሚቴው ስራውን የጀመረ ስለሆነ፤ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለባንኩ ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ብቁ እጩዎች እስከ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ እንዲጠቁሙኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ተጠቋሚዎች በእጩነት ለመቅረብ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1. የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ፤
  2. የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
  3. የማንኛውም ባንክ ሰራተኛ ያልሆነ፤
  4. እድሜው 30 አመትና ከዚያ በላይ የሆነ፤
  5. በወጋገን ባንክ አ.ማ. የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭኮሚቴ አባል ያልሆነ፤
  6. በሌላ የገንዘብ ተቋም ውስጥ የዲሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ፤
  7. የመምረጥና የመመረጥ መብቱ ያልተገደበ፤
  8. በስነ-ምግባሩም ሆነ ድርጊቱ ህዝብን ከማታለልና ማጭበርበር ለመጠበቅ ሲባል የወጣን ህግ በመተላለፍ በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭየተፈረደበት መሆኑን የሚያሳይ ሪኮርድ ወይም ማስረጃ የሌለበት፤
  9. ስልጣን ላለው ተቆጣጣሪ አካል መስጠት ያለበትን መረጃ በመደበቅ፣ ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት፣ ማሟላት ያለበትን መስፈርት ባለማሟላቱ ምክንያት የእርምት እርምጃ የተወሰደበት መሆኑን የሚያሳይ ሪኮርድ የሌለበት፤
  10. የፋይናንሺያልጤናማነት (nancial soundness) መስፈርት የሚያሟላ ማለትም ኪሳራ ላይ ያልሆነ፣ የተበደረውን የባንክ እዳ መክፈል የቻለ፣ ግብር ባለመክፈሉ ምክንያት ያልተፈረደበት፣ በቂ ስንቅ /ገንዘብ/ የሌለው ቼክ ያልጻፈ፤
  11. የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ያለው፤
  12. የሥራ ልምድን በተመለከተ ቢቻል በንግድ ስራና በንግድ ስራ አስተዳደር በተለይም በፋይናንስ ተቋም ወይም በባንክ የስራ ልምድ ያለው፤

ማሳሰቢያ

  1. በጠቅላላው እጩየቦርድ ተጠቋሚዎች ብዛት 22 ነው፡፡ ከሚጠቆሙት 22 እጩዎች መካከል ስምንቱ ከባንኩ ጠቅላላ የተፈረሙአክሲዮኖች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 2% (ሁለት በመቶ) በታች የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች ብቻ ሲሆኑ፤ መጠቆም የሚችሉትም ከባንኩ ጠቅላላ የተፈረሙአክሲዮኖች ውስጥ በቀጥታም ሆነ
    በተዘዋዋሪ 2% (ሁለት በመቶ) በታች ባላቸው ባለአክሲዮኖች ብቻ ነው፡፡ የቀሪዎቹን 14 እጩዎች ጥቆማ በተመለከተ ሁሉም ባለአክሲዮኖች ሊጠቁሙና ሊጠቆሙይችላሉ፤
  2. መስፈርቱን የሚያሟላና ፈቃደኛ የሆነ ባለአክሲዮን ራሱን መጠቆም ይችላል፤
  3. የህግ ሰውነት ያለው ባለአክሲዮን በእጩነት ሊጠቆምና ዕጩሊጠቁም ይችላል፤
  4. ማንኛውም ጥቆማ ሲቀርብ የጠቋሚውሙሉስምና ፊርማ ሊኖረው ይገባል፤
  5. በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴት ጾታም ያገለግላል፤
  6.  ከመስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

ስለዚህ የባንኩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ ለዲሬክተሮች ቦርድ ዕጩዎችን ለመጠቆም የተዘጋጀውን ቅጽ ከባንካችን ዋና መስሪያ ቤት፣ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ቅርንጫፍ መ/ቤት፣ ንኡስ ቅርንጫፍ ወይም ከባንኩ ድረ ገጽ www.wegagen.com በመውሰድ ለዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭኮሚቴ በሚከተሉት መንገዶች ጥቆማ እንድታቀርቡ መጋበዛችሁን እናሳውቃለን፡፡

  1. በአዲስ አበባ፣ ወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና መ/ቤት ሕንጻ፣ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ
    ኮሚቴ ቢሮ በግንባር በመቅረብ፤ ወይም
  2. ከአዲስ አበባ ውጭየሚገኙ ባለአክሲዮኖች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንካችን ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ወይም ቅርንጫፍ መ/ቤት በግንባር ተገኝተው ጥቆማቸውን ማቅረብ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡ 0911270415፣ 0911202758 ወይም 0911152492 መደወል ይቻላል፡፡

የወጋገን ባንክ አ.ማ. የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ

About the Author

Comments are closed.